prayer request

Go back

Your message has been sent

Warning
Warning
Warning
Warning

Warning.

ለደበዘዙ ቀኖቼ (በጣም) አጭር ጸሎት

ለደበዘዙ ቀኖቼ (በጣም) አጭር ጸሎት

ልቤ ሊደበዝዝ ድርቅ ሲል እና ሲደክም መዝሙር 51 ላይ ወደሚገኝ የዳዊት መዝሙር ዘወር እላለሁ።

የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሺታ መንፈስም ደግፈኝ” (መዝሙር 51፡12) ።

ይሄ ክፍል በቃል ለመያዝ ቀላል ከመሆኑ በላይ ነፍሴ ድክም ስትል ጸሎቴን ትኩረት እንድሰጠው ያደርገኛል ። የጸሎቱ መዋቅር በየዕለቱ የሚያስፈልጉኝ የሦስት ነገሮች ልመና ነው ።

ደስታዬን አድስ፡- እግዚአብሔር ሆይ ኃጢያተኛ ነፍሴን ለማዳን የወሰድከውን ርቀት አስታውሰኝ ። ባዳነኝ ጣፋጭ ምህረት እደሰት ዘንድ እባክህ ይገባኝ የነበረውን ቅዱሱን ቁጣህን ዳግም አስታውሰኝ ። ይህ ደስታ አሁን የሚሰማኝን መድከም እንዲሸፍን አድርግ ። 

ታማኝነቴን መልስ፡- እግዚአብሔር ሆይ ልቤ የዛለው ታማኝነቴ ልክ ስላልሆነ ነው ። ልቤን ባዶ የሚያደርጉትን ቀለል ያሉ ነገሮችን ፤ ድሎትን እና የሰው ምስጋናን ፈልጌአለሁ ። ኃጢያቴን አምናለሁ እባክህን ታማኝነቴን ከስምህ ጋር አንድ ላይ አስሂድ ። ለክብርህም መልሼ መሰጠት እንድችል አድርግ ። “የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” (መዝሙር 51፡10)

የእሽታ ታዛዥነትን ስጠኝ፡- እግዚአብሔር ሆይ በግዴታዎች ተነሳስቼ ሳይሆን ውስጤ ባለው በሚያስችለው መንፈስህ ዛሬ እንድታዘዝህ እርዳኝ ። ልታዘዝህ እና የመታዘዝን የደስታ ፍሬ መቅመስ ከልቤ እፈልጋለሁ ። ነፃ የሆነ እሺ የሚል መንፈስ ያስፈልገኛል ። የአንተን ነፃ እና እሺ የሚል መንፈስ እሻለሁ። በእዚህ እንድትደግፈኝ እጸልያለሁ። 

በእራሴ ቋንቋ፡- እግዚአብሔር ሆይ ደስታዬን አድስ ፣ ታማኝነቴን መልስ እናም ዛሬ አንተን እንድታዘዝ ነፃነትን ስጠኝ ።

ደብዛዛ በሆኑ ቀኖቼ ዞር ብዬ የማያቸው በጣም አጭር ጸሎቶቼ እነዚህ ናቸው ።